Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 10:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሕግ ወደ ፊት ለሚመጣው መልካም ነገር ምሳሌ (ጥላ) ነበር እንጂ እውነተኛ መልኩ አልነበረም፤ ስለዚህ በየዓመቱ ዘወትር የሚሠዉትን መሥዋዕቶች ይዘው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሰዎች ፍጹሞች ሊያደርጋቸው ከቶ አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሕጉ ወደ ፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ ነው እንጂ እውነተኛው አካል አይደለም፤ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር ያለ ማቋረጥ የሚቀርበው ተደጋጋሚ መሥዋዕት፣ ለአምልኮ የሚቀርቡትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው ከቶ አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሕጉ ወደ ፊት ለሚመጣው መልካም ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን ጥላ በመሆኑ፥ እውነተኛ አካል አይደለም። በየዓመቱም ዘወትር በሚያቀርቡት መሥዋዕት የሚቀርቡትን ለፍጽምና ሊያበቃ ከቶ አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እው​ነ​ተኛ አም​ሳል ሳይ​ሆን የነ​ገር ጥላ አለ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በየ​ዓ​መቱ ዘወ​ትር በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት በዚያ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊፈ​ጽም ከቶ አይ​ች​ልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 10:1
13 Referencias Cruzadas  

ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርበውንም እንስሳ አምጥቶ በሥርዓቱ መመሪያ ሕግ መሠረት ሠዋው።


ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።


እነዚህ ሁሉ ወደፊት ይመጡ ለነበሩት ነገሮች እንደ ጥላ ናቸው፤ እውነቱ የሚገኘው ግን በክርስቶስ ነው።


ስለዚህ ከክፉ ኅሊና እንድንነጻ ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፥ ቅን ልብና እውነተኛ እምነት ይዘን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።


እንግዲህ ለሕዝቡ ሕግ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ነው፤ በዚህ በሌዋውያን ክህነት ፍጹምነት ቢገኝ ኖሮ የአሮን የክህነት ሹመት ሳይሆን የመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት ያለው ሌላ ካህን መምጣት ባላስፈለገም ነበር፤


እነዚህ ካህናት የሚያገለግሉበት ድንኳን በሰማይ ለሚገኘው ምሳሌና ጥላ ብቻ ነው፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኒቱን በሚሠራበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር “በተራራው ላይ እንደ ተገለጠልህ ዐይነት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ አድርግ” ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው።


ነገር ግን ክርስቶስ በመምጣት ላይ ላሉት መልካም ነገሮች የካህናት አለቃ ሆኖ ተገልጦአል፤ እርሱ የገባባት ድንኳን ትልቅና ፍጹም ናት፤ ይህች ድንኳን በሰው እጅ ያልተሠራችና ከዚህ ፍጥረት ያልሆነች ናት።


እንግዲህ እነዚህ የሰማያዊ ነገሮች ምሳሌ የሆኑት ሁሉ በዚህ ዐይነት ሥርዓት መንጻት ያስፈልጋቸው ነበር፤ ከሰማይ የሆኑት ነገሮች ግን ከዚህ በሚበልጥ መሥዋዕት መንጻት ያስፈልጋቸዋል።


የአይሁድ የካህናት አለቃ የራሱ ያልሆነውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባ ነበር፤ ክርስቶስ ግን ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ አልገባም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos