Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 38:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ለድንኳኑና በዙሪያው ላለው የአደባባይ አጥር መጋረጃዎች የሚያገለግሉት ካስማዎች ሁሉ የተሠሩት ከነሐስ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የማደሪያው ድንኳንና የአደባባዩ ዙሪያ ካስማዎች ሁሉ ከንሓስ የተሠሩ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የማደሪያውና በዙሪያው ያለ የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የድ​ን​ኳ​ኑም ካስ​ማ​ዎች፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ የአ​ደ​ባ​ባዩ ካስ​ማ​ዎች የናስ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የማደሪያውም ካስማዎች በዙሪያውም ያለ የአደባባዩ ካስማዎች የናስ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 38:20
10 Referencias Cruzadas  

ምስማሮቹን ለማሠራት አምስት መቶ ሰባ ግራም ወርቅ ፈጅቶበታል፤ የፎቁ ክፍሎች ግንቦችም በወርቅ ተለብጠው ነበር።


አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።


በድንኳኑ ውስጥ የሚገኙት ለማናቸውም ጥቅም የሚውሉ የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።


አራት የነሐስ እግሮች ባሉአቸው አራት ምሰሶዎች ተደግፎ ነበር፤ ኩላቦቻቸው፥ ጫፎቻቸውና ዘንጎቻቸው ከብር የተሠሩ ነበሩ፤


በሙሴ ትእዛዝ፥ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት የሌዋውያን ተግባር የሆነው የተቀደሰው ድንኳን ዕቃዎች ዝርዝር ቈጠራ እነዚህ ናቸው፦


የጠቢባን ንግግር፥ እረኛ የከብቶቹን መንጋ እንደሚነዳበት ጫፉ እንደ ሾለ በትር ነው፤ በአንድነት የተከማቹ ምሳሌዎች ጠልቀው እንደሚገቡ ምስማሮች ናቸው፤ እነርሱም ከሁላችን ጠባቂ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸው።


እኔ እርሱን ኲላብ ተብሎ እንደሚጠራ እንደ ጠንካራ የዕቃ መስቀያ አደርገዋለሁ፤ ለቤተሰቡ ሁሉ የክብር መገኛ ይሆናል።


የታወቁ የሃይማኖት በዓላትን የምናከብርባትን የጽዮንን ከተማ ተመልከቱ፤ በሰላም ትኖሩባት ዘንድ ምቹ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን እዩ! ካስማዎቹ ከቶ እንደማይነቀሉ፥ ገመዶቹም እንደማይበጠሱና ከስፍራው እንደማይንቀሳቀስ ድንኳን ትሆናለች።


እንዲህ ያለ ሰው ራስ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ አካልን በሙሉ በመገጣጠሚያና በጅማት አያይዞ የሚመግበው ራስ ነው። እግዚአብሔር ለአካል ሙሉ ዕድገት የሚሰጠውም በዚህ ዐይነት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos