Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 20:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ለእኔ የድንጋይ መሠዊያ ማበጀት ብትፈልጉ ከጥርብ ድንጋይ የተሠራ አይሁን፤ የብረት መሣሪያ ቢነካው ታረክሱታላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከድንጋይ መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ፣ ከጥርብ ድንጋይ አትሥራ፤ መሣሪያ የነካው ከሆነ ታረክሰዋለህና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የድንጋይም መሠዊያ ብታደርግልኝ በተጠረበ ድንጋይ አትሥራው፤ በመሣሪያ ብትነካው ታረክሰዋለህና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የድ​ን​ጋ​ይም መሠ​ዊያ ብታ​ደ​ር​ግ​ልኝ ጠር​በህ አት​ሥ​ራው፤ በመ​ሣ​ሪያ ብት​ነ​ካው ታረ​ክ​ሰ​ዋ​ለ​ህና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የድንጋይም መሠዊያ ብታደርግልኝ ብረት በነካው ድንጋይ አትሥራው፤ በመሣሪያ ብትነካው ታረክሰዋለህና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 20:25
6 Referencias Cruzadas  

ቤተ መቅደሱ የታነጸባቸው ድንጋዮች ተጠርበው የተዘጋጁት፤ በዚያው በተፈለጡበት ቦታ ነበር፤ ስለዚህም ቤተ መቅደሱ በሚሠራበት ጊዜ የመዶሻ፥ የመጥረቢያ ወይም የሌላ ብረት ነክ መሣሪያ ድምፅ አይሰማም ነበር።


ለእኔ ከጭቃ የተሠራ መሠዊያ አብጁልኝ፤ በእርሱም ላይ ከበጎቻችሁ፥ ከፍየሎቻችሁና ከከብቶቻችሁ መርጣችሁ የሚቃጠልና የአንድነት መሥዋዕት አድርጋችሁ ሠዉበት፤ ስሜ እንዲታሰብበት በወሰንኩት ስፍራ ሁሉ ወደ እናንተ መጥቼ እባርካችኋለሁ፤


ሙሴም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጻፈ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ በተራራው ሥር መሠዊያ ሠራ፤ ለእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንድ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤


እንደዚሁም ለሚቃጠለው መሥዋዕት ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ አራት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ ርዝመታቸው አንድ ክንድ ተኩል ወርዳቸው አንድ ክንድ ተኩል፥ ከፍታቸው አንድ ክንድ ነበር፤ እነርሱም ለሚቃጠለውና ለሌሎች መሥዋዕት የማረጃ ዕቃዎች ማስቀመጫነት የሚያገለግሉ ነበሩ።


የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እስራኤላውያንን ባዘዘው መሠረት በሙሴ አማካይነት በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ ውስጥ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና ብረት ባልነካው ድንጋይ መሠዊያ ሠርተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት ቊርባን አቀረቡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos