Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አስቴር 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲያውም የየሀገሩ ገዢዎችና አስተዳዳሪዎች ሌሎችም ባለሥልጣኖችና የመንግሥት ተወካዮች ሁሉ አይሁድን ረዱአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት መርዶክዮስን በመፍራት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የየአውራጃው መኳንንት ሁሉ፣ እንደራሴዎች፣ የአውራጃ ገዦች እንዲሁም የንጉሡ አስተዳዳሪዎች አይሁድን ረዷቸው፤ ይህን ያደረጉትም መርዶክዮስን ስለ ፈሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 መርዶክዮስን መፍራት በላያቸው ስለ ወደቀ በየአገሩ የነበሩ አዛውንትና ሹማምቶች አለቆችም፥ የንጉሡንም ሥራ የሚሠሩቱ ሁሉ አይሁድን አገዙ።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 9:3
9 Referencias Cruzadas  

ለተመለሱትም ስደተኞች መሪዎች ሆነው የመጡት ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ሠራያ፥ ረዔላያ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፓር፥ ቢግዋይ፥ ሬሁምና በዓና ተብለው የሚጠሩት ነበሩ። ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ጐሣ በመሰባሰብ ወደ ሀገር የተመለሱትም ስደተኞች ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦


ንጉሠ ነገሥቱ የሰጣቸውንም ሰነድ በኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ላሉት ገዢዎችና ባለሥልጣኖች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ በማገዝ ድጋፋቸውን ሰጡ።


ስለዚህ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ሃማን የንጉሡን ጸሐፊዎች ጠርቶ ዐዋጁ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተተርጒሞ፥ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በሚገኘው የአጻጻፍ ሥርዓት ሁሉ በመዘጋጀት፥ ወደ አገረ ገዢዎችና ወደ ባለሥልጣኖች ሁሉ እንዲላክ ያደርጉ ዘንድ አዘዘ፤ ዐዋጁም በንጉሥ አርጤክስስ ስም ተጽፎ የቀለበቱ ማኅተም ተደርጎበት ተላለፈ።


በየትኛውም አገርና በማንኛይቱም ከተማ የንጉሡ ዐዋጅ በተነበበበት ስፍራ ሁሉ በአይሁድ ዘንድ ተድላና ደስታ ሆነ፤ በዚሁ ምክንያት አይሁድን ከመፍራት የተነሣ ከሌሎች አሕዛብ ወገኖች ብዙዎቹ የአይሁድን ሃይማኖት ተቀበሉ።


“የግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድ ቢሆንና ስለ እኔም የሚያስብልኝ ከሆነ፥ እንዲሁም ጉዳዩ በእርስዎ ፊት ትክክል ሆኖ ከተገኘ፥ በንጉሠ ነገሥት ግዛትዎ ሁሉ ውስጥ የሚገኙ አይሁድ ሁሉ ይደመሰሱ ዘንድ የአጋግ ዘር የነበረው የሃመዳታ ልጅ ሃማን ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ የሚሽር ዐዋጅ እንዲያስተላልፉልኝ እለምንሃለሁ።


ይህም የሆነው ሲዋን ተብሎ የሚጠራው ሦስተኛ ወር በገባ በሃያ ሦስተኛው ቀን ነበር፤ መርዶክዮስ የንጉሡን ጸሐፊዎች ሁሉ ጠርቶ ለአይሁድ፥ ከሕንድ እስከ ኢትዮጵያ ያሉትን መቶ ኻያ ሰባት አገሮች ለሚያስተዳድሩ አገረ ገዢዎችና ሌሎችም ባለሥልጣኖች የሚላኩ ደብዳቤዎችን አስጻፈ፤ ደብዳቤዎቹም በእያንዳንዱ አገር ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት እንዲሁም በአይሁድ ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትለው እንዲጻፉ ተደረገ።


የቆመው ምስል በሚመረቅበት ክብረ በዓል ላይ እንዲገኙ አገረ ገዢዎችን መኳንንትን፥ ሹማምንትን፥ አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኀላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ ሌሎችንም የየክፍለ ሀገሩ ባለሥልጣኖችን አስጠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos