አስቴር 7:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እነሆ እኔና ወገኖቼ ለባርነት መሸጥ አንሶን ለመገደልና ለመደምሰስ ቀርበናል፤ ለባርነት ከመሸጥ የከፋ ነገር ባይደርስብን ኖሮ፥ ዝም ባልኩና እርስዎን ለማስቸገር ባልደፈርኩ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ልንጠፋና ከምድር ገጽ ልንደመሰስ ተፈርዶብናል!” ስትል መለሰችለት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እኔና ሕዝቤ ለጥፋት፣ ለዕርድና ለመደምሰስ ተሸጠናልና። ወንዶችና ሴቶች ባሮች ለመሆን የተሸጥን ቢሆን ኖሮ፣ ዝም ባልሁ ነበር፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ጭንቀት ንጉሡን ለማስቸገር የሚበቃ አይደለም።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እኔና ሕዝቤ ለመጥፋትና ለመገደል ለመደምሰስም ተሸጠናልና። ባርያዎች ልንሆን ተሸጠን እንደ ሆነ ዝም ባልሁ ነበር፥ የሆነ ሆኖ ጠላቱ የንጉሡን ጉዳት ለማቅናት ባልቻለም ነበር አለች። Ver Capítulo |