Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አስቴር 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የአይሁድን ሕዝብ ለማስፈጀት በሱሳ ከተማ የተላለፈውን የዐዋጅ ቅጂም ለሀታክ ሰጠው፤ ይህንኑ የዐዋጅ ቅጂ ወስዶ ለአስቴር እንዲሰጣትና የሆነውንም ነገር ሁሉ እንዲገልጥላት፥ እንዲሁም ወደ ንጉሡ ዘንድ ገብታ ስለ ሕዝብዋ ምሕረትን እንድትለምን ይነግራት ዘንድ ሀታክን ለመነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አይሁድን ለማጥፋት በሱሳ የወጣውን የዋናውን ዐዋጅ ቅጅም ለአስቴር እንዲያሳያትና በዝርዝር እንዲያስረዳት ሰጠው፤ ወደ ንጉሡም ዘንድ ገብታ ስለ ሕዝቧ ምሕረት እንድትጠይቅና እንድትማልድ አጥብቆ ይነግራት ዘንድ አሳሰበው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ለአስቴርም እንዲያሳያት ለመጥፋታቸው በሱሳ የተነገረውን የአዋጁን ጽሕፈት ቅጅ ሰጠው፥ ወደ ንጉሡም ገብታ ስለ ሕዝብዋ ትለምነውና ትማልደው ዘንድ እንዲነግራትና እንዲያዝዛት ነገረው።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 4:8
14 Referencias Cruzadas  

አስቴርም አይሁዳዊት መሆንዋን ገና አላስታወቀችም ነበር፤ መርዶክዮስም ይህን ለማንም እንዳትናገር በጥብቅ አስጠንቅቆአት ነበር፤ እርስዋም በሕፃንነትዋ ጊዜ በእርሱ ኀላፊነት ሥር ሳለች በሁሉ ነገር ትታዘዘው እንደ ነበር አሁንም በዚህ ነገር ታዘዘችለት።


ሀታክም ይህን ሁሉ ፈጸመ፤


ይህ ሁሉ ጥፋት በሕዝቤ ላይ ሲደርስና የገዛ ዘመዶቼም ሲገደሉ እንዴት መታገሥ እችላለሁ?”


ንጹሕ ሆኜ ብገኝ እንኳ፥ ፈራጁ አምላክ እንዲምረኝ እለምነዋለሁ እንጂ መልስ ልሰጠው አልደፍርም።


በኢየሩሳሌም ከተማ ሰላም እንዲሆን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ “የሚወዱሽ ሁሉ ይበልጽጉ፤


የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱንም እንደ ወራጅ ውሃ ወደ ፈቀደው ይመራዋል። የንጉሥንም አእምሮ ይቈጣጠራል።


ጸጥ ብለህ ብትታገሥ ከባድ ለሆነው በደልህ እንኳ ይቅርታ ማግኘት ስለምትችል አለቃህ በተቈጣህ ጊዜ የሥራ ቦታህን አትልቀቅ፤


ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቈጥቶ ነበር፤ እነርሱም በአንድነት መጡና፤ የንጉሥ ባለሟል ብላስጦስ እንዲተባበራቸው ለምነው እሺ ካሰኙትም በኋላ ንጉሡን ዕርቅ ጠየቁ፤ ይህንንም ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበረ ነው።


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው ጲላጦስ ፊት በመልካም መታመን በመሰከረው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝሃለሁ።


የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos