Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አስቴር 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከቀን ወደ ቀን ሐሳቡን ለማስቀየር ይጥሩ ነበር፤ እርሱ ግን ሊሰማቸው አልወደደም፤ እንዲያውም እኔ አይሁዳዊ ስለ ሆንኩ ለሃማን መስገድ አይገባኝም በማለት ቊርጥ ውሳኔውን ገለጠላቸው ከዚህ በኋላ የመርዶክዮስን ትዕቢት እንዴት መታገሥ ይቻላል? እያሉ በመገረም ጉዳዩን ለሃማን ነገሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ይህንም በየቀኑ ይነግሩት ነበር፤ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም። አይሁዳዊ መሆኑን ነግሯቸው ስለ ነበር፣ የመርዶክዮስ ባሕርይ እስከ መቼ ሊቀጥል እንደሚችል ለማየት ሲሉ ይህንኑ ለሐማ ነገሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ይህንም ዕለት ዕለት እየተናገሩ እርሱ ባልሰማቸው ጊዜ አይሁዳዊ እንደ ሆነ ነግሮአቸው ነበርና የመርዶክዮስ ነገር እንዴት እንደ ሆነ ያዩ ዘንድ ለሐማ ነገሩት።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 3:4
11 Referencias Cruzadas  

እርስዋም ይህንኑ ጉዳይ በየቀኑ ትነግረው ነበር፤ ዮሴፍ ግን አብሮአት መተኛት ወይም በአጠገቧ ለመገኘት አልፈለገም።


ከእናንተ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነ ሁሉ፥ አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በይሁዳ ወደሚገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ይሥራ።


በቤተ መንግሥት ሥራ ላይ የተመደቡ ሌሎች ባለሥልጣኖች መርዶክዮስን “የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ?” እያሉ፥


ሃማንም መርዶክዮስ ተንበርክኮ የማይሰግድለት መሆኑን ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።


እነሆ፥ በባቢሎን አውራጃዎች ላይ ገዢዎች አድርገህ የሾምካቸው ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ የተባሉ የአይሁድ ወገኖች የአንተን ትእዛዝ አይፈጽሙም፤ አማልክትህን አያመልኩም፤ ላቆምከውም ምስል አይሰግዱም።”


እነርሱም “እንግዲያውስ ንጉሥ ሆይ! ከይሁዳ ምርኮኞች አንዱ የሆነው ዳንኤል አንተን አያከብርህም፤ ፈርመህበት የወጣውንም ዐዋጅ በመጣስ በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ ይጸልያል” አሉት።


ዮናስም “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን የሰማይ አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” ሲል መለሰላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos