Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አስቴር 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እርሱም በዕብራይስጥ ሀዳሳ የተባለችውን የአጐቱን ልጅ አስቴርን ያሳድግ ነበር፤ እርስዋም ቁመናዋ የተስተካከለ እጅግ ውብ ልጃገረድ ነበረች፤ ወላጆችዋም ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ መርዶክዮስ ወደ ቤቱ በመውሰድ ልክ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ በመንከባከብ አሳደጋት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 መርዶክዮስ አንዲት ሀደሳ የምትባል የአጎቱ ልጅ ነበረችው፤ አባትና እናት ስላልነበራት ያሳደጋት እርሱ ነበር። አስቴር ተብላ የምትጠራው ይህች ልጃገረድ በተክለ ሰውነቷም ሆነ በመልኳ እጅግ ውብ ነበረች። አባቷና እናቷ ከሞቱ በኋላ መርዶክዮስ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ ወሰዳት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አባትና እናትም አልነበራትምና የአጎቱ ልጅ ሀደሳ የተባለችውን አስቴርን አሳድጎ ነበር፥ ቆንጆይቱም የተዋበችና መልከ መልካም ነበረች፥ አባትዋና እናትዋም ከሞቱ በኋላ መርዶክዮስ እንደ ልጁ አድርጎ ወስዶአት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 2:7
12 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ልጄ ዮሴፍ እኔ እዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለት ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ናቸው፤ ኤፍሬምና ምናሴ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ይቈጠራሉ።


“ንግሥት አስጢን ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳና ዘውድ ጭና ወደዚህ እንድትመጣ አድርጉ” አላቸው፤ ንጉሡ ይህንን ያደረገበት ምክንያት ንግሥት አስጢን እጅግ የተዋበች ስለ ነበረች ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖችና ለእንግዶቹ ሁሉ እንድትታይ ፈልጎ ነበር።


በዚህ ዐይነት አስቴር ወደ ንጉሡ ፊት የምትቀርብበት ጊዜ ደረሰ፤ ይህችም አስቴር የአቢኀይል ልጅ፥ እንደ ልጁ አድርጎ ያሳደጋት የመርዶክዮስ የአጐት ልጅ የነበረችውና ባያት ሁሉ ዘንድ ሞገስን ያገኘች ነበረች፤ እርስዋም ወደ ንጉሡ ፊት የመቅረብ ተራዋ በደረሰ ጊዜ የለበሰችው፥ የምርጥ ሴቶች መኖሪያ ቤት ኀላፊ የነበረው ጃንደረባው ሄጋይ እንድትለብስ የመከራትን እንጂ እርስዋ የጠየቀችውን ልብስ አልነበረም።


አስቴርም አይሁዳዊት መሆንዋን ገና አላስታወቀችም ነበር፤ መርዶክዮስም ይህን ለማንም እንዳትናገር በጥብቅ አስጠንቅቆአት ነበር፤ እርስዋም በሕፃንነትዋ ጊዜ በእርሱ ኀላፊነት ሥር ሳለች በሁሉ ነገር ትታዘዘው እንደ ነበር አሁንም በዚህ ነገር ታዘዘችለት።


ንጉሥ አርጤክስስ የአይሁድ ጠላት የነበረውን የሃማንን ሀብት በሙሉ በዚያኑ ዕለት ለአስቴር ሰጣት፤ አስቴርም፥ መርዶክዮስ ለእርስዋ የቅርብ ዘመድ መሆኑን ለንጉሡ ነገረችው፤ መርዶክዮስም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወደ ንጉሡ ፊት መቅረብ ተፈቀደለት፤


የሙት ልጆች እየራባቸው ምግቤን ብቻዬን አልበላሁም።


ነገር ግን ከወጣትነቴ ጀምሬ እንደ አባት ሆኜላቸዋለሁ፤ በሕይወቴ ዘመኔ ሁሉ ባልዋ የሞተባትን ረድቼአለሁ።


እኔ አባታችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፥ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።”


እናንተም ወላጆች ሆይ! በጌታ በኢየሱስ ሥነ ሥርዓትን በማስተማር፥ በማረምና በመገሠጽ አሳድጉአቸው እንጂ ልጆቻችሁን በማስቈጣት አታስመርሩአቸው።


የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ! በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀ እኛንም አያውቀንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos