መክብብ 8:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በምድር ላይ የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፤ አንዳንድ ጊዜ ደጋግ ሰዎች ለክፉ ሰዎች የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ ክፉ ሰዎች ደግሞ ለደጋግ ሰዎች የሚገባውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው አልኩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 በምድር ላይ የሚከሠት ሌላም ከንቱ ነገር አለ፤ ጻድቃን ለክፉዎች የሚገባውን፣ ክፉ ሰዎችም ለጻድቃን የሚገባውን ይቀበላሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ነው አልሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በክፉዎች ላይ የሚደረገው የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው የሚደርስላቸው ክፉዎችም አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ከፀሓይ በታች በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው ሥራ የሚደርስላቸው ኃጥኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኀጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው ሥራ የሚደርስላቸው ኀጥኣን አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ። Ver Capítulo |