Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 14:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አሳ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አሳ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አሳም በአምላኩ በጌታ ፊት መልካምና ቅን ነገር አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አሳም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ቅን ነገር አደ​ረገ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አሳም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን ነገር አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 14:2
15 Referencias Cruzadas  

አሳ፥ የቀድሞ አያቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ።


ንጉሥ አሳ በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የቤተ ጣዖትን አመንዝራዎችን ሁሉ ከሀገሪቱ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖቶችንም ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ።


አሳ በኰረብቶች ላይ የሚገኙ የአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎችን በሙሉ ባያስወግድም እንኳ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ኖረ።


ንጉሥ አቢያ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሳ ነገሠ፤ በአሳም ዘመነ መንግሥት በምድሪቱ ላይ ለዐሥር ዓመት ሰላም ሆነ፤


ባዕዳን መሠዊያዎችንና በኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን አስወገደ፤ ለማምለኪያ የተሠሩ የድንጋይ ዐምዶችን ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎችን አንከታክቶ ጣለ፤


አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራ የሴት አምላክ አጸያፊ ምስል ስላቆመች፥ ንጉሥ አሳ ከእተጌነትዋ ሻራት፤ ምስሉንም ሰባብሮ አደቀቀው፤ ስብርባሪውንም በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው፤


እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ አገለገለ፤ ከዚህም በላይ በኰረብቶች ላይ የሚገኙትን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችንና በይሁዳ የነበሩትን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎች ሁሉ ደመሰሰ።


ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ እንደ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አደረገ፤


ከዚህ በኋላ ነቢዩ ኤልያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ለኢዮራም ላከ፦ “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአባትህን የንጉሥ ኢዮሣፍጥን ወይም የአያትህን የንጉሥ አሳን መልካም ምሳሌነት አልተከተልክም፤


ከበዓሉ ፍጻሜ በኋላ መላው የእስራኤል ሕዝብ ወደ ይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመሄድ ከድንጋይ የተሠሩትን የጣዖት ዐምዶች ሰባበሩ፤ አሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የቆሙ ምስሎችንም ሰባብረው ጣሉ፤ መሠዊያዎችንና የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎችንም ደመሰሱ፤ እንዲሁም በቀሩት በይሁዳ፥ በብንያም፥ በኤፍሬምና በምናሴ ግዛቶች ውስጥ የነበሩትን የጣዖት መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን ሁሉ አፈራረሱ፤ ከዚያም በኋላ ወደየመኖሪያ ስፍራዎቻቸው ተመለሱ።


ንጉሥ ሕዝቅያስ በመላው የይሁዳ ግዛት መልካም የሆነውንና ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አደረገ፤


የሰሜን የእስራኤል ግዛት የነበሩትን የጣዖቶች መሠዊያዎችንና የአሼራ ምስሎችን ሁሉ ሰባበራቸው፤ ጣዖቶቹንም ትቢያ እስኪሆኑ አደቀቃቸው፤ ዕጣን የሚታጠንባቸውንም የጣዖት መሠዊያዎች አንከታክቶ ጣለ፤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።


ለእነርሱ አማልክት በመንበርከክ አትስገድ፤ አታምልካቸው፤ ሃይማኖታዊ ልማዶቻቸውንም አትከተል፤ አማልክታቸውን አጥፋ፤ ለእነርሱ ቅዱሳን የሆኑትን የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም አፈራርስ፤


እንዲሁም በሕይወታችን ዘመን ሁሉ፥ በእግዚአብሔር ፊት በቅድስናና በጽድቅ መኖር እንድንችል ነው።


መሠዊያዎቻቸውን ሁሉ አፈራርሱ፤ ከድንጋይ የተሠሩ የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውንም አድቅቁ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላካቸውን ምስሎች ሁሉ በእሳት አቃጥሉ፤ የተቀረጹ ጣዖቶቻቸውን ሰባብሩ፤ ስሞቻቸውንም ከቦታቸው አጥፉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos