Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 8:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 “ጠላቶቻቸውን ለመውጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 “ሕዝብህ ጠላታቸውን ለመውጋት አንተ ወደምትልካቸው ወደ የትኛውም ቦታ ለጦርነት በሚወጡበት ጊዜ፣ አንተ ወደ መረጥሃት ከተማና እኔ ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 “ጠላቶቻቸውን ለመውጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 “ሕዝ​ብ​ህም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ለመ​ው​ጋት አንተ በም​ት​መ​ል​ሳ​ቸው መን​ገድ ቢወጡ፥ አን​ተም ወደ መረ​ጥ​ሃት ከተማ፥ እኔም ለስ​ምህ ወደ ሠራ​ሁት ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቢጸ​ልዩ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 “ሕዝብህም ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ቢወጡ፥ አንተም ወደ መረጥሃት ከተማ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤት ለእግዚአብሔር ቢጸልዩ፥

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 8:44
26 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም “በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልባቸውን? ድልንስ ትሰጠኛለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ በእነርሱ ላይ አደጋ ጣልባቸው! እኔ በእነርሱ ላይ ድልን እሰጥሃለሁ!” ሲል መለሰለት።


ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት “አሁን ካለህበት በኩል በእነርሱ ላይ አደጋ አትጣል፤ ነገር ግን ከወዲያ በኩል በስተ ኋላ በመዞር ከሾላ ዛፎች ፊት ለፊት ሆነህ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ።


‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዐይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጬአለሁ።’ ”


በሰማይም ሆነህ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በመስማት ዓላማቸውን ደግፍ።


ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ስለ መሰላቸው በእርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከበቡት፤ ነገር ግን ኢዮሣፍጥ ጮኸ፤ እግዚአብሔር አምላክም ከእነርሱ እጅ በመታደግ አዳነው፤ እነርሱም በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተገቱ።


ከኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች ጋር በአንድነት ሆነው በቤተ መቅደሱ አዲስ አደባባይ ተሰበሰቡ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥም መጥቶ በሕዝቡ ፊት ቆመ፤


ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ፤ እንዲረዳቸውም ወደ እርሱ አጥብቀው ጮኹ፤


“ጠላቶቻቸውን ለመውጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፥


ዳንኤል ዐዋጁ ተፈርሞበት እንደ ጸና ቢያውቅም እንኳ ወደሚኖርበት ሰገነት ወጣ፤ የሚኖርበትም ሰገነት በኢየሩሳሌም ትይዩ የተከፈቱ መስኮቶች ነበሩት፤ ከዚህ በፊት ያደርገው እንደ ነበረም በጒልበቱ በመንበርከክ አምላኩን እያመሰገነ በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልይ ነበር።


የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ሂድ፤ በዚህ ባለህ ብርቱ ኀይል ሁሉ በመጠቀም እስራኤላውያንን ከምድያማውያን እጅ ነጻ አውጣ፤ እነሆ እኔ ራሴ ልኬሃለሁ” ሲል አዘዘው።


ኃጢአተኞች የሆኑትን እነዚያን አማሌቃውያንን እንድትደመስስ ልኮሃል፤ እስኪጠፉም ድረስ እነርሱን ግደል ብሎ ነግሮሃል።


ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።”


ዳዊትም “እነዚያን ወራሪዎች ተከታትዬ በማሳደድ ልያዛቸውን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ተከተላቸው! እነርሱንም ይዘህ ምርኮኞችን በመታደግ ታድናለህ” ሲል መለሰለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos