Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 2:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ከከተማይቱ ወጥተህ የቄድሮንን ወንዝ ተሻግረህ ብትገኝ በእርግጥ ትሞታለህ፤ ለደምህም ተጠያቂ ራስህ ነህ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ነገር ግን ከዚያ ወጥተህ የቄድሮንን ሸለቆ ከተሻገርህ እንደምትሞት ዕወቅ፤ ደምህም በራስህ ላይ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ከከተማይቱ ወጥተህ የቄድሮንን ወንዝ ተሻግረህ ብትገኝ በእርግጥ ትሞታለህ፤ ለደምህም ተጠያቂ ራስህ ነህ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 በም​ት​ወ​ጣ​በ​ትና የቄ​ድ​ሮ​ን​ንም ፈፋ በም​ት​ሻ​ገ​ር​በት ቀን ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ሞት ዕወቅ፤ ደም​ህም በራ​ስህ ላይ ይሆ​ናል።” ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ አማ​ለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 በወጣህበትም ቀን፥ የቄድሮንንም ፈፋ በተሻገርህበት ቀን ፈጽመህ እንድትሞት እወቅ፤ ደምህ በራስህ ላይ ይሆናል፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 2:37
13 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።


የዳዊት ተከታዮች ወጥተው በሄዱ ጊዜ ሕዝቡ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ንጉሡ ከተከታዮቹ ጋር የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ በአንድነትም ሆነው ወደ በረሓው አመሩ።


አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሻራት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው።


ሰሎሞንም በናያን እንዲህ አለው፦ “ኢዮአብ እንዳለህ ግደለውና ቅበረው፤ በዚህ አኳኋን ኢዮአብ ካፈሰሰው ንጹሕ ደም በደል የእኔንና የአባቴን ቤት የነጻን አድርገን።


ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ በእርሱ ላይ የተፈጸመበት ቅጣት በእርሱና በዘሮቹ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር፤ በዙፋኑ ላይ ለሚቀመጡት ለዳዊት ዘሮች ግን የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም አይለያቸው።”


ሺምዒም “ንጉሥ ሆይ! ውሳኔህ ትክክል ነው፤ እኔ አገልጋይህ አንተ ጌታዬ እንዳልከው አደርጋለሁ” ሲል መለሰ፤ ስለዚህ በኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ ተቀመጠ።


አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ከቤተ መቅደስ ነቅሎ ከከተማይቱ በማውጣት ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ትቢያ እስኪሆንም አድቅቆ፥ በሕዝብ መቃብር ላይ በተነው።


ካህናቱም ቤተ መቅደሱን ለማንጻት ወደ ውስጡ ገቡ፤ ያልነጻውንም ነገር ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ አወጡት፤ ሌዋውያኑም ከዚያ አንሥተው ከከተማ ውጪ በመውሰድ በቄድሮን ሸለቆ ጣሉት።


በድንና ዐመድ የሚጣልበት መላው ሸለቆ በምሥራቅ በኩል እስከ ፈረስ በር ድረስ እንኳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከተማይቱም እንደገና ከቶ አትፈርስም፤ አትደመሰስምም።”


ገንዘቡን በአራጣ ቢያበድርና ከፍተኛ ወለድ ቢያስከፍል፥ ታዲያ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት ሊኖር ይችላልን? ከቶ በሕይወት ሊኖር አይችልም፤ ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር በማድረጉ በእርግጥ ይሞታል፤ ለሞቱም ተጠያቂው እርሱ ራሱ ይሆናል።


ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ይገደል፤ አባቱንና ወይም እናቱን ስለ ሰደበ ሞት የተፈረደበት በራሱ በደል ነው።


ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ቄድሮን ሸለቆ ማዶ ሄደ፤ እዚያ ወደነበረውም የአትክልት ቦታ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ገባ።


ማንም ከቤት ወጥቶ ቢገኝና ቢሞት ጥፋቱ የራሱ ይሆናል፤ እኛም በኀላፊነት አንጠየቅም፤ ከአንቺ ጋር በቤት ሳለ ማንም ሰው ጒዳት ቢደርስበት ግን በኀላፊነት ተጠያቂዎች ነን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos