Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 12:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባኤአቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረም የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢዮርብዓም መመለሱን እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ጉባኤያቸው በማስጠራት በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት። ለዳዊት ቤት በታማኝነት ጸንቶ የተገኘው የይሁዳ ቤት ብቻ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባኤአቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረም የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከዚ​ህም በኋላ እስ​ራ​ኤል በሙሉ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከግ​ብፅ እንደ ተመ​ለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸን​ጎ​አ​ቸው ጠሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሡት። ከብ​ቻው ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ነገድ በቀር የዳ​ዊ​ትን ቤት የተ​ከ​ተለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም እንደ ተመለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸንጎአቸው ጠሩት፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሡት። ከብቻው ከይሁዳ ነገድ በቀር የዳዊትን ቤት የተከተለ አንድ ሰው አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 12:20
12 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም እስራኤላውያን ዳዊትን ከድተው ከሼባዕ ጋር ሄዱ፤ የይሁዳ ሕዝብ ግን ታማኝነታቸውን በማጽናት ከዮርዳኖስ እስከ ኢየሩሳሌም ዳዊትን ተከትለው ሄዱ።


ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”


በሰሎሞን ላይ ያመፀው ሌላው ሰው በኤፍሬም ጸሬዳ ተብላ የምትጠራው ክፍል ተወላጅ የሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነው፤ እርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች አንዱ ነበር፤ እናቱም ጽሩዓ ተብላ የምትጠራ ባልዋ የሞተባት ሴት ነበረች።


ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ።


ስለዚህ መንግሥትን ከሰሎሞን ልጅ ወስጄ ለአንተ ዐሥሩን ነገድ እሰጥሃለሁ፤


ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ


ኢዮርብዓም ሆይ! እኔ አንተን የእስራኤል ንጉሥ አደርግሃለሁ፤ አንተ በወደድከው ግዛት ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ።


ሮብዓምም በይሁዳ ግዛት በሚኖሩት ሕዝብ ላይ ብቻ ነገሠ።


እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተዉ በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ በሐሰትና በማታለል ከበውኛል፤ ይሁዳ ግን አሁንም እኔ በእግዚአብሔር በምመራው መንገድ ይሄዳል፤ ለእኔ ለቅዱሱም ታማኝ ነው።


“ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤ እኔን ሳይጠይቁ መሳፍንትን መርጠው ሾሙ፤ ከብራቸውና ከወርቃቸው ለገዛ ራሳቸው መጥፊያ የሆኑትን ጣዖቶችን ሠሩ።


ሳሙኤልም ሕዝቡን “እግዚአብሔር የመረጠው ሰው እነሆ ይህ ነው! ከእኛም መካከል እርሱን የሚስተካከለው የለም” አለ። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos