Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሳኦልን ራስ ቈርጠው የጦር መሣሪያውን ከገፈፉ በኋላ በመልእክተኞች አስይዘው የምሥራቹን ለአማልክታቸውና ለሕዝባቸው ይነግሩላቸው ዘንድ ላኩአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሳኦልን ከገፈፉ፣ ራሱን ከቈረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ ለጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲናገሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ገፈፉትም፥ ራሱንና መሣሪያውንም አንሥተው ለጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራች እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ዙሪያ መልእክተኞችን ላኩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሳኦ​ል​ንም ገፈ​ፉት፥ ራሱ​ንም ቈር​ጠው መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም አን​ሥ​ተው ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ለሕ​ዝቡ የም​ሥ​ራች ይወ​ስዱ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ዙሪያ ሰደዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ገፈፉትም፤ ራሱንና መሣሪያውንም አንሥተው ለጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምስራች ይወስዱ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ዙሪያ ሰደዱ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 10:9
9 Referencias Cruzadas  

የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፥ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ ይህን ወሬ በጋት አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ አታውጁ።


የሳኦልን የጦር መሣሪያዎች በአማልክታቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩ፤ ራሱንም ዳጎን ተብሎ በሚጠራው አምላካቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ሰቀሉት።


እርሱም በዚህ ጊዜ ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ አረማውያን መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ይህን ለማድረግ እጅግ ስለ ፈራ አላደረገውም፤ ስለዚህም ሳኦል የራሱን ሰይፍ መዞ በመሬት ላይ በመትከል በላዩ ላይ ወደቀ፤


በጦርነቱ ማግስት ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን እስራኤላውያን ለመግፈፍ በሄዱ ጊዜ የሳኦልና የልጆቹ ሬሳ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተጋድሞ አገኙ፤


ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ከቤተ መቅደሱ ተዘርፈው የመጡትን የወርቅ ዕቃዎች አስመጥተህ አንተና መኳንንቶችህ፥ ሚስቶችህና ቁባቶችህ የወይን ጠጅ መጠጫ አደረጋችኋቸው፤ ከጠጣችሁም በኋላ ማየት ወይም መስማት የማይችሉትንና ምንም ነገር የማያውቁትን ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት አመሰገናችሁ፤ መግደል ወይም ማዳን የሚችለውንና አካሄድህን የሚቈጣጠረውን ሕያው አምላክ ግን አላከበርከውም።


የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን አምጥተው ለልጅቱ ሰጡአት፤ እርስዋም ለእናትዋ ወስዳ ሰጠች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos