Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 36:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በምድር ላይ ባፈሰሱት ደምና በጣዖቶቻቸውም አርክሰዋታልና መዓቴን አፈሰስሁባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ስለዚህ በምድሪቱ ላይ ደም ስላፈሰሱና በጣዖታቶቻቸው ስላረከሷት፣ መዓቴን አፈሰስሁባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በሀገሪቱ ላይ ስለ ፈጸሙት ግድያና በጣዖት አምልኮም ምድሪቱን በማርከሳቸው ምክንያት ኀይለኛ ቊጣዬን አወረድኩባቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በም​ድር ላይ ስለ አፈ​ሰ​ሱት ደም፥ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስለ አረ​ከ​ሱ​አት መዓ​ቴን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በምድር ላይ ስላፈሰሱት ደም በጣዖቶቻቸውም ስላረከሱአት መዓቴን አፈሰስሁባቸው፥

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 36:18
21 Referencias Cruzadas  

“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለማድረግ አባቶቻችን የጌታን ቃል ስላልጠበቁ፥ በእኛ ላይ የነደደው የጌታ ቁጣ እጅግ ታላቅ ነውና ሄዳችሁ ስለ ተገኘው የመጽሐፍ ቃል ለእኔ በእስራኤልና በይሁዳም ለቀሩት ጌታን ጠይቁ።”


በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት ዐጥነዋልና ቁጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።


ጌታን ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ ሰማኸው ቃላት፥


ስለዚህ የቁጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰባቸው፤ በዙሪያቸውም አነደደው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፥ አቃጠላቸውም እነርሱ ግን ልብ አላሉም።


ምድሬንም በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”


ስለዚህ መዓቴና ቁጣዬ ወረዱ፥ በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ነደዱ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ፈረሱ ባድማም ሆኑ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቁጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይወርዳል፤ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።”


ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።


ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፥ ጽኑ ቁጣውን አፍስሶአል፥ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፥ መሠረትዋንም በላች።


ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ ቁጣዬን በደም ባፈስስባትና ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ ባጠፋ፥


ቁጣዬንም አፈስስብሃለሁ፥ በመዓቴም እሳት አነድብሃለሁ፥ ማጥፋትንም ለሚያውቁ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።


ሰው ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቆርቆሮንም ለማቅለጥ እሳትን ሊያነድበት በማቅለጫ እንደሚሰበስብ፥ እንዲሁ በቁጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ።


ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጡዋ ትቀልጣላችሁ፥ እኔም ጌታ መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።


አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፤ ከጣዖቶቻቸው ጋር አመንዝረዋል፤ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆቻቸውን እንኳ መብል እንዲሆኑ አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል።


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?


የእስራኤል ቤት በበደላቸው ምክንያት እንደ ተማረኩ አሕዛብ ያውቃሉ፤ እኔን ስለ በደሉኝ፥ እኔም ፊቴን ከእነርሱ ሰወርሁ፥ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ።


አሁን በቅርብ መዓቴን በአንቺ ላይ አፈስሳለሁ፥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ እፈጽማለሁ፥ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፥ ርኩሰትሽንም ሁሉ እመልስብሻለሁ።


በቁጣው ፊት ማን ይቆማል? የቁጣውንስ ንዳድ ማን ይቋቋማል? መዓቱ እንደ እሳት ፈሰሰ፤ ከእርሱ የተነሣ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ።


እርሱ ደግሞ በቁጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos