ሕዝቅኤል 35:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በእስራኤል ተራሮች ላይ “ፈርሰዋል እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ ጌታ እንደ ሰማሁት ታውቃለህ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ከዚያም ስለ እስራኤል ተራሮች፣ “ጠፍ ሆነዋል፤ ቦጫጭቀን እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ በንቀት የተናገርኸውን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁ በዚያ ጊዜ ታውቃለህ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 እነርሱ ባድማ የተደረጉ ስለ ሆነ በእኛ ቊጥጥር ሥር እንዲሆኑ ተሰጥተውናል’ ብላችሁ በእስራኤል ተራራዎች ላይ የተናገራችሁትን የንቀት ንግግር እኔ እግዚአብሔር የሰማሁ መሆኔን ወደፊት ታውቃላችሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አንተም፦ ፈርሰዋል፤ መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል ብለህ በእስራኤል ተራሮች ላይ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁት ታውቃለህ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አንተም፦ ፈርሰዋል መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል ብለህ በእስራኤል ተራሮች ላይ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁት ታውቃለህ። Ver Capítulo |