Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 34:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከእነርሱ ጋር የሰላምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፥ ክፉ አራዊትን ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ በሰላምም በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘ከእነርሱ ጋራ የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚያም ምድሪቱን ከዱር አራዊት ነጻ አደርጋለሁ፤ እነርሱም በምድረ በዳ ይኖራሉ፤ በደንም ውስጥ ያለ ሥጋት ይተኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የሰላም ዋስትና የሚያገኙበትን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ፤ አደገኞች የሆኑትን አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ ስለዚህ በጎቼ በየመስኩ በሰላም ተሰማርተው ሊኖሩና በየጫካውም ሊያድሩ ይችላሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “የሰ​ላ​ም​ንም ቃል ኪዳን ከዳ​ዊት ቤት ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድር አጠ​ፋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም በም​ድረ በዳ ይኖ​ራሉ፤ በዱ​ርም ውስጥ ይተ​ኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የሰላምን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ ክፉዎችንም አራዊት ከምድር አጠፋለሁ፥ ተዘልለውም በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 34:25
31 Referencias Cruzadas  

በጥፋት አደጋና በራብ ላይ ትስቃለህ፥ የምድረ በዳ አራዊትንም አትፈራም፥


ቃል ኪዳንህ ከምድረበዳ ድንጋይ ጋር ይሆናልና፥ የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር ይስማማሉና።


በልቤ ደስታን ጨመርህ፥ ከስንዴ ፍሬያቸውና ከወይናቸው ይልቅ በዛ።


በተኛህ ጊዜ አትፈራም፥ ስትተኛም፥ እንቅልፍህ የጣፈጠ ይሆንልሃል።


አንበሳም አይኖርበትም፥ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፥ እነዚህ ከዚያ አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤


ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል የሚራራልሽ ጌታ።


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


እኔ ጌታ ፍትህን የምወድ፥ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።


የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነርሱም አንድም አይጐድልም፥ ይላል ጌታ።


በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም በደኅንነት ይቀመጣል፥ እርሱም፦ ‘ጌታ ጽድቃችን ነው’ በሚለው በዚህ ስም የሚጠራ ይሆናል።


እነሆ፥ በቁጣዬና በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፥ በደኅንነትም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤


በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም በደኅንነት ትቀመጣለች፤ እርሷም፦ ‘ጌታ ጽድቃችን ነው’ በሚለው ስም ትጠራለች።


ነገር ግን በልጅነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር የመሠረትኩትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፥ የዘለዓለምንም ቃል ኪዳን አቆማለሁ።


ቃል ኪዳኔን ከአንቺ ጋር አቆማለሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቂያለሽ፤


ከበትርም በታች አሳልፋችኋለሁ ወደ ቃል ኪዳንም እስራት አገባችኋለሁ፤


ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ ወይኑንም ይተክላሉ በዙሪያቸውም ባሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን ባደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም ጌታ አምላካቸው እንደሆንሁ ያውቃሉ።


የሜዳ ዛፍም ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፥ በምድራቸውም በሰላም ይኖራሉ፤ የቀንበራቸውንም ዘንግ ስሰብር ከሚገዙአቸውም እጅ ሳድናቸው፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ከእንግዲህም ለሕዝቦች ብዝበዛ አይሆኑም፥ የምድርም አራዊት አይበሉአቸውም፤ በሰላም ይኖራሉ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።


የሰላም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፤ አጸናቸዋለሁ፥ አበዛቸዋለሁ፥ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘለዓለም አኖራለሁ።


ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘለዓለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርሷም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።


ማንም ሳያስፈራቸው በምድራቸው በሰላም በተቀመጡ ጊዜ፥ እፍረታቸውንና የበደሉኝን በደላቸውን ይሸከማሉ።


ምድሪቱም ፍሬዋን ትሰጣለች፥ እስክትጠግቡም ድረስ ትበላላችሁ፤ በእርሷም ላይ በደኅንነት ትቀመጣላችሁ።


ለእናተም እህሉን ማበራየቱ የወይኑን ዘለላ እስከሚቆረጥበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፥ የወይኑንም ዘለላ መቁረጥ እህል እስከ ሚዘራበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፤ እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፥ በምድራችሁም ላይ በደኅንነት ትቀመጣላችሁ።


በምድሪቱም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራራችሁ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።


ከተማዋም ሰዎች ይኖሩባታል፥ ከዚያም ወዲያ እርግማን አይኖርም። ኢየሩሳሌምም በሰላም ትኖራለች።


እርሱ የጌታን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይጐናጸፋል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ መግባባት ይኖራል።


ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፥ የሰላም ቃል ኪዳኔን እሰጠዋለሁ።


በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos