ሕዝቅኤል 33:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ዘበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ አይቶ መለከቱን ባይነፋ፥ ሕዝቡን ባያስጠነቅቅ፥ ሰይፍም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኃጢአቱ ተወስዶአል ደሙን ግን ከዘበኛው እጅ እፈልጋለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ነገር ግን ጕበኛ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ፣ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ሳይነፋ ቢቀርና ከመካከላቸው የአንዱን ሰው ሕይወት ሰይፍ ቢያጠፋ፣ ያ ሰው ስለ ኀጢአቱ ይወሰዳል፤ ጕበኛውን ግን ስለ ሰውየው ደም ተጠያቂ አደርገዋለሁ።’ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ነገር ግን ጠባቂው ጠላት ሲመጣ እያየ ከአደጋ ማስጠንቀቂያውን ድምፅ ሳያሰማ ቢቀር፥ ጠላት መጥቶ ከእነዚያ መካከል አንዱን ቢገድል ያ ሰው የሞተው በኀጢአቱ ነው፤ እኔ ግን ስለ እርሱ ለደሙ ኀላፊ አድርጌ የምጠይቀው ጠባቂውን ነው።’ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ጕበኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለከቱንም ባይነፋ፥ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኀጢአቱ ተወስዶአል፤ ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ጕበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ ቢያይ መለከቱንም ባይነፋ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ ሰይፍም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኃጢአቱ ተወስዶአል ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ። Ver Capítulo |