ሕዝቅኤል 23:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ሴሰኝነትሽንና ከግብጽ ምድር ያመጣሽውን ዝሙትሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፥ ዓይንሽን ወደ እነርሱ አታነሺም፥ ግብጽንም ዳግም አታስቢም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 በግብጽ የጀመርሽውን ብልግናና ሴሰኛነት ከአንቺ አስወግዳለሁ፤ አንቺም ዐይንሽን ወደ እነዚህ አታነሺም፤ ከእንግዲህ ግብጽን አታስቢም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 የዝሙት ሥራሽንና ገና በግብጽ ሳለሽ ጀምሮ የምትፈጽሚያቸውን አሳፋሪ ድርጊቶች ሁሉ እንድትተይ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም ወደ ጣዖቶች አትመለከቺም፤ ስለ ግብጽም አታስቢም።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ሴሰኝነትሽንም፥ ከግብፅ ምድር ያወጣሽውን ዝሙትሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፤ ዐይንሽንም ከእንግዲህ ወዲህ ወደ እነርሱ አታነሺም፤ ግብፅንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ሴሰኝነትሽንም፥ ከግብጽ ምድር ያወጣሽውን ግልሙትናሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፥ ዓይንሽንም ወደ እነርሱ አታነሺም ግብጽንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም። Ver Capítulo |