Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 20:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ወደ አሕዛብ ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ‘የሕዝቦች በረሓ’ ተብላ ወደምትጠራ ምድር አመጣችኋለሁ፤ በዚያም ዐይናችሁ እያየ እፈርድባችኋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ወደ አሕ​ዛ​ብም ምድረ በዳ አመ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ፊት ለፊት ከእ​ና​ንተ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 20:35
19 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፥ አላዋቂዎች ዘወትር የተሳለቁብህን አስብ።


ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤


አንቺ ግን፦ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእውነት ቁጣው ከእኔ ተመልሶአል’ አልሽ። እነሆ፦ ‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና በፍርድ እከስሻለሁ።


“ስለዚህ ከእናንተ ጋር ገና እከራከራለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ።


ጌታ ከአሕዛብ ጋር ሙግት አለውና ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል ጌታ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ።


መረቤን በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ፥ በዚያም በእኔ ላይ ለፈጸመው ክሕደት ከእርሱ ጋር እፋረዳለሁ።


አሁንም በምድረ በዳ፥ በደረቅና በተጠማ መሬት ተተከለች።


በግብጽ ምድረ በዳ ከአባቶቻችሁ ጋር እንደ ተፋረድሁ እንዲሁ ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍና የበረዶ ድንጋይ፥ እሳትና ዲን በእርሱና በወታደሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉት ብዙ ሕዝቦች ላይ አዘንባለሁ።


ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘለዓለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርሷም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።


እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጪ፥ ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትቀመጫለሽና፥ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፤ በዚያ ትድኛለሽ፥ በዚያም ጌታ ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።


ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኩሌታ ወደምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሓ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።


አሁንም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ጌታ ስላደረገው የጽድቅ ሥራ ሁሉ በጌታ ፊት ስለምሟገታችሁ በዚህ ቁሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos