Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 23:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ፥ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ እናንተም ወደ እነርሱ እነርሱም ወደ እናንተ ብትደራረሱ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ነገር ግን ከርሱ ተመልሳችሁ ተርፈው በመካከላችሁ ከሚገኙት ከእነዚህ ሕዝቦች ጋራ ብትተባበሩ፣ በጋብቻም ብትተሳሰሩና ብትቀላቀሉ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ፥ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ እናንተም ከእነርሱ እነርሱም ከእናንተ ጋር በጋብቻ ቢተሳሰሩ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እናንተ ግን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ በእናንተ መካከል ከቀሩት ከእነዚህ ሕዝቦች ጋር ብትተባበሩ፥ እናንተ የእነርሱን ሴቶች እነርሱ ደግሞ የእናንተን ሴቶች በመጋባት ብትተሳሰሩ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እና​ንተ ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ብት​ጠጉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ብት​ጋቡ፥ እና​ን​ተም ወደ እነ​ርሱ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ ብት​ደ​ራ​ረሱ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 23:12
28 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሰዉ አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ በሚስቱም ይጣበቃ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።


ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ ብላቴናይቱንም ወደዳት ልብዋንም ደስ በሚያስኛት ነገር ተናገራት።


እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች “አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፤ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ፤” ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ።


ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም።


ኃጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች ዘር፥ ርኵሰትን የምታደርጉ ልጆች ሆይ፥ ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ትተዋል የእስራኤልንም ቅዱስ አቃልለዋል ወደ ኋላቸውም እየሄዱ ተለይተዋል።


ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ ኃጢአትንም ቢሠራ ኃጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም፥ ባደረገው ዓመፅና በሠራት ኃጢአት በዚያች ይሞታል።


እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።


ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።


ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤


ከእነርሱም ጋር አትጋባ፤ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ፥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ።


እንዳይከተለኝ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል።


አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱት ዘንድ ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ።


በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።


አባቱና እናቱም፦ ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለማግባት ትሄድ ዘንድ ከወንድሞችህ ሴቶች ልጆች ከሕዝቤም ሁሉ መካከል ሴት የለምን? አሉት። ሶምሶንም አባቱን፦ ለዓይኔ እጅግ ደስ አሰኝታኛለችና እርስዋን አጋባኝ አለው።


ሴት ልጆቻቸውንም አገቡአቸው፥ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፥ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos