Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዩኤል 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፥ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፥ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በፊታቸው፣ እሳት ይባላል፤ በኋላቸውም ነበልባል ይለበልባል፤ በፊታቸው ምድሪቱ እንደ ዔድን ገነት ናት፤ በኋላቸውም የሚቀረው ባዶ ምድረ በዳ ነው፤ ምንም አያመልጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፥ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፥ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነርሱ በፊታቸው የሚገኘውን ተክል ሁሉ እንደ እሳት ይበላሉ፤ እንደ ነበልባልም ያቃጥላሉ። ገና ያልደረሱበት፥ በፊታቸው ያለው ምድር፥ እንደ ዔደን የአትክልት ቦታ የለመለመ ነው፤ እነርሱ ያለፉበት ምድር ግን የወደመ በረሓ ይሆናል፤ ከእነርሱ የሚያመልጥ ምንም ነገር አይገኝም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እሳት በፊ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ለች፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ል​ባል ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ሪቱ በፊ​ታ​ቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእ​ር​ሱም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዩኤል 2:3
21 Referencias Cruzadas  

ሎጥም ዓይኑን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።


እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።


የምድሩንም ፊት ፈጽመው ሸፈኑት፤ አገሪቱም ጨለመች፤ የአገሪቱን ቡቃያ ሁሉ በረዶውም የተወውን በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በሉ፤ ለምለም ነገር ዛፍም የምድር ሣርም በግብፅ አገር ሁሉ አልቀረም።


የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፤ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፤


ዓለሙን ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችንም ያፈረሰ፥ ምርኮኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።


የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፥ ሣሩም ደርቋል፥ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም።


አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፥ ኩብኩባም እንደሚዘልል ሰዎች ይዘልሉበታል።


እግዚአብሔርም ጽዮንን ያጽናናል፥ በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፥ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔድን በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል፥ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።


ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፥ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፥ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል።


በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ተቃጥላለች፥ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፥ ሰውም ለወንድሙ አይራራም።


መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፥ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፥ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፥ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።


ሰዎችም፦ ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፥ የፈረሱት ባድማ የሆኑት የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ፥ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።


እነሆ፥ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ።


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፥ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos