“እጄን በይሁዳ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤ የበኣልን ትሩፍ፣ የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤
በሰማርያ ላይ ያዘጋጀሁትን መለኪያ ገመድ፣ የአክዓብንም ቤት የለካሁበትን ቱንቢ በኢየሩሳሌም ላይ እዘረጋለሁ፤ አንድ ሰው ሳሕን እንደሚወለውል ከወለወለም በኋላ እንደሚገለብጠው እኔም ኢየሩሳሌምን ወልውዬ እገለብጣታለሁ።
የይሁዳ ነገሥታት በላይኛው የአካዝ እልፍኝ አጠገብ በሰገነቱ ላይ ያቆሟቸውን መሠዊያዎች፣ ምናሴም በሁለቱ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባዮች ላይ ያሠራቸውን መሠዊያዎች አስወገደ፤ ስብርብራቸውን አወጣ፤ ድቃቂውንም አንሥቶ ወደ ቄድሮን ሸለቆ ጣለው።
በርሱም ትእዛዝ የበኣሊም መሠዊያዎችን አፈራረሱ፤ እርሱም ከበላያቸው የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎችን አደቀቀ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶችን፣ ጣዖታቱንና ምስሎቹን ሰባብሮ ከፈጫቸው በኋላ፣ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብር ላይ በተነ።
“ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።
እኔን ጥለሽኛል” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ ኋላም እያፈገፈግሽ ነው፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ አጠፋሻለሁም፤ ከእንግዲህም አልራራልሽም።
በምድሪቱ በሚኖሩት ላይ እጄን በምዘረጋበት ጊዜ፣ ዕርሻቸውና ሚስቶቻቸው ሳይቀሩ፣ ቤቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።
ክንዴን በእናንተ ላይ አነሣለሁ፤ በአሕዛብ እንድትበዘበዙ አደርጋለሁ፤ ከሕዝቦች መካከል አውጥቼ፣ ከአገሮችም ለይቼ አጠፋችኋለሁ፤ እደመስሳችኋለሁም። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”
እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ የሚኖሩበትንም ስፍራ ከምድረ በዳው እስከ ዴብላታ ድረስ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤ ያን ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣ በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ ሕዝቡም ያለቅስለታል፤ በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣ አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤ በምርኮ ከእነርሱ ተወስዷልና።
የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣ የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራ አትሰግዱም።
እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለርሱ ይሰግዳሉ።
እጁን በሰሜን ላይ ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌን ፍጹም ባድማ፣ እንደ ምድረ በዳም ደረቅ ያደርጋታል።