ድብልቅ ሕዝቦች አዛጦንን ይይዛሉ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ትምክሕት እቈርጣለሁ።
ሰው ልቡ የሚሻውን እንዳያጣ፣ አምላክ ባለጠግነትን፣ ሀብትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ አምላክ ግን እንዲደሰትበት ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይልቁን ባዕድ ይደሰትበታል። ይህም ከንቱ፣ እጅግም ክፉ ነገር ነው።
የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣ በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኗል።
ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፣ በለመለመ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት ለሆነች ጠውላጋ አበባ፣ የወይን ጠጅ ለዘራቸው መኵራሪያ ለሆነች፣ ለዚያች ከተማ ወዮላት!
ፈርዖን ጋዛን ድል ከማድረጉ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
የሰማይ አምላክ የሚያደርገው ሁሉ ትክክል፣ መንገዶቹም ሁሉ ጽድቅ ስለ ሆኑ፣ አሁንም እኔ ናቡከደነፆር እርሱን አወድሰዋለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ አከብረዋለሁም፤ እርሱም በትዕቢት የሚመላለሱትን ማዋረድ ይችላል።
በአስቀሎና በትር የያዘውን፣ የአሽዶድንም ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ በፍልስጥኤም ካሉት የመጨረሻው ሰው እስኪሞት ድረስ፣ እጄን በአቃሮን ላይ እዘረጋለሁ፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሰድበው ዘብተውበታልና፣
ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤ አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤ አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤ አቃሮንም ትነቀላለች።
አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤ አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና። ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አቃሮንም ባድማ ትሆናለች።
ደሙን ከአፋቸው፣ አስጸያፊውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ። የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤ በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።
ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”