ቀስቴን እንደ ገተርሁ፣ ይሁዳን እገትረዋለሁ፤ ኤፍሬምንም ፍላጻ አደርገዋለሁ። ጽዮን ሆይ፤ ልጆችሽን አስነሣለሁ፤ ግሪክ ሆይ፤ በአንቺ ልጆች ላይ ይነሣሉ፤ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።
እጆቼን ለጦርነት፣ ጣቶቼን ለውጊያ የሚያሠለጥን፣ እግዚአብሔር ዐለቴ ይባረክ።
የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣ ባለሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤
ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ።
አፌን እንደ ተሳለ ሰይፍ አደረገው፤ በእጁ ጥላ ሰወረኝ፤ የተወለወለ ፍላጻ አደረገኝ፤ በሰገባውም ውስጥ ሸሸገኝ።
“አንቺ የእኔ ቈመጥ፣ የጦር መሣሪያዬ ነሽ፤ በአንቺ ሕዝቦችን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ መንግሥታትን አጠፋለሁ፤
እንደ ወርቅ ይቈጠሩ የነበሩ፣ የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች፣ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣ እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ!
“ደግሞም ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ መካከል፣ ናዝራውያንንም ከጕልማሶቻችሁ መካከል አስነሣሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ ይህ እውነት አይደለምን?” ይላል እግዚአብሔር።
የዔሳውን ተራሮች ለመግዛት፣ ነጻ አውጪዎች ወደ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።
እኔም፣ “እነዚህስ ምን ሊያደርጉ መጡ?” አልሁ። እርሱም፣ “እነዚህ ቀንዶች ማንም ራሱን ቀና ማድረግ እንዳይችል ይሁዳን የበታተኑ ናቸው፤ እነዚህ የእጅ ሙያተኞች ግን የመጡት እነርሱን ሊያስደነግጧቸው፣ ሕዝቡን ለመበታተን በይሁዳ ምድር ላይ ቀንዳቸውን ያነሡትን የእነዚህን የአሕዛብ ቀንዶች ሰብሮ ለመጣል ነው” አለኝ።
የመዳንን ራስ ቍር አድርጉ፤ የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖትንም ጠብቄአለሁ።
የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል።
በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሓይ ነበረ።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከርሱ ጋራ ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ዐብረው ድል ይነሣሉ።”
ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ወጣ፤ “በብረት በትርም ይገዛቸዋል።” እርሱም ሁሉን ቻይ የሆነውን የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣ ወይን መጭመቂያ ይረግጣል።
የቀሩት ደግሞ በፈረሱ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው በልተው ጠገቡ።
“በጴርጋሞን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል።