እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ጊዜ ይህ ለቀረው የእስራኤል ሕዝብ አስደናቂ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ ለእኔ ግን አስደናቂ ሊሆን ይችላልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።”
ንጉሡ በክንዱ ላይ የተደገፈውም የጦር አለቃ፣ የእግዚአብሔርን ሰው፣ “እንዲያው ለመሆኑ፣ እግዚአብሔር የሰማያትን መስኮቶች ቢከፍት እንኳ ይህ ሊሆን ይችላልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም፣ “ይህን አንተው ራስህ በዐይንህ ታየዋለህ፤ ይሁን እንጂ ከዚያ አንዳች አትቀምስም” አለው።
እግዚአብሔር ይህን አድርጓል፤ ይህም ለዐይናችን ድንቅ ነው።
“አቤት፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰማያትንና ምድርን በታላቅ ኀይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፤ የሚሳንህም አንዳች ነገር የለም።
“እነሆ፤ እኔ የሰው ልጆች ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ የሚያቅተኝ ነገር አለን?
ኢየሱስም አያቸውና፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉም ነገር ይቻላል” አላቸው።
እነሆ፤ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፣ ይህም እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም።”
ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።”
ኢየሱስም፣ “በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል” አለ።