Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘካርያስ 5:9

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ከፊቴ ሁለት ሴቶች ነበሩ፤ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበር፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወፎች ጐጇቸውን በዚያ ይሠራሉ፤ ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች።

ሽመላ እንኳ በሰማይ፣ የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፤ ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም፣ የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ሕዝቤ ግን፣ የእግዚአብሔርን ሥርዐት አላወቀም።

“መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ! ሕዝቡ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፣ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና፣ ንስር በእግዚአብሔር ቤት ላይ ነው፤

“ ‘ከአዕዋፍ ወገን እነዚህን ትጸየፋላችሁ፤ ጸያፍ ስለ ሆኑም አትብሏቸው፦ ንስር፣ የጥንብ አሞራ፣ ግልገል አንሣ፣

ሽመላ፣ ማንኛውም ዐይነት ሳቢሳ፣ ጃንጁላቴ ወፍና የሌሊት ወፍ።

ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረውንም መልአክ፣ “ቅርጫቱን የሚወስዱት ወዴት ነው?” አልሁት።

በድን ባለበት ስፍራ ሁሉ አሞሮች ይሰበሰባሉ።

እግዚአብሔር እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋውን የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፣ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች