እንደ ገናም ተመለከትሁ፤ በዚያም በፊቴ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ትልቅ ሰሌዳ ወስደህ፣ ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’ ብለህ በተለመደው በሰው ፊደል ጻፍበት።
እርሱም፣ “ምን ታያለህ?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም፣ “ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ዐሥር ክንድ የሆነ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አያለሁ” አልሁት።
በእጁም የተከፈተች ትንሽ ጥቅልል መጽሐፍ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፣ ግራ እግሩን በምድር ላይ አኖረ፤