እርሱም፣ “ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።
እንደ ገናም፣ “በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈስሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።
ያነጋግረኝ የነበረውንም መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው” አልሁት።
መልአኩም መልሶ፣ “ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።