ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተግራ ያሉት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።
እንደ ገናም፣ “በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈስሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።
ደግሞም አንዱ ከዘይቱ ማሰሮ በስተቀኝ፣ ሌላውም በስተግራ የሆኑ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”
እነዚህም በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙት ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።