የጥድ ዛፍ ሆይ፤ ዝግባ ወድቋልና አልቅስ፤ የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋል! የባሳን ወርካዎች ሆይ፤ አልቅሱ፤ ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሯል!
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ደቡብ አዙር፤ በደቡብ ላይ ቃል ተናገር፤ በደቡብ አገር ደን ላይም ትንቢት ተንብይ።
ከባሳን በመጣ ወርካ፣ መቅዘፊያሽን ሠሩ፤ ከቆጵሮስ ጠረፍ በመጣ ዝግባ፣ በዝኆን ጥርስ ለብጠው ወለልሽን ሠሩ።
ከአሕዛብ መካከል ከርሱ ጋራ ያበሩ፣ በጥላው ሥር የኖሩ፣ በሰይፍ ከሞቱት ጋራ ለመቀላቀል ወደ መቃብር ወርደዋል።
በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣ በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣ እናንተ የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!
ሊባኖስ ሆይ፤ እሳት ዝግባሽን እንዲበላው ደጆችሽን ክፈቺ!
የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ ክብራቸው ተገፍፏልና፤ የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል!
እንግዲህ በርጥብ ዕንጨት እንዲህ ካደረጉ፣ በደረቁ ምን ያደርጉ ይሆን?”