Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘካርያስ 1:7

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ ሳባጥ በሚባለው በዐሥራ አንደኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”

በምሽት ራእይ አየሁ፤ እዚያም በፊቴ አንድ ሰው በቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጧል፤ እርሱም በሸለቆ ውስጥ በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ ነበር፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቡናማና ነጭ ፈረሶች ነበሩ።

ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ፣ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች