አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?
በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ለሞት ባደረሰው ሕመም ታምሞ ነበር። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ወርዶ አለቀሰለት፤ “ወየው አባቴን! ወየው አባቴን! ወየው የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” እያለም ጮኸ።
ኤልሳዕ ሞተ፤ ቀበሩትም። በዚህም ጊዜ ሞዓባውያን አደጋ ጣዮች በየዓመቱ በጸደይ ወራት ወደ እስራኤል ምድር እየሰረጉ ይገቡ ነበር።
የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን።
ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
ዳገት መውጣት ሲያርድ፣ መንገድም ሲያስፈራ፣ የአልሙን ዛፍ ሲያብብ፣ አንበጣም ራሱን ሲጐትት፣ ፍላጎት ሲጠፋ፤ በዚያም ጊዜ ሰው ወደ ዘላለማዊ ቤቱ ይሄዳል፤ አልቃሾችም በአደባባዮች ይዞራሉ።
ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።
“ሌላ ብራና ወስደህ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው በመጀመሪያው ብራና ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ጻፍበት፤
አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው ዐለፉ፤ እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።
አይሁድም እንዲህ አሉት፤ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ማንም ቃልህን ቢጠብቅ ሞትን ፈጽሞ እንደማይቀምስ ትናገራለህ።
“ዳዊት በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካገለገለ በኋላ አንቀላፍቷል፤ ከአባቶቹም ጋራ ተቀብሮ ሥጋው በስብሷል።
ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል።
ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ አርማቴም ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።