“እግዚአብሔር በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቶ ነበር፤
ለርግማንና ለጥፋት የተዳረጉ ስለ መሆናቸው በዚህ ስፍራና በሕዝቡ ላይ የተናገርኩትን በሰማህ ጊዜ ልብህ ስለ ተነካና በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ስላዋረድህ፣ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል እግዚአብሔር።
ይህም ሆኖ እንኳ ለቍጣ እንዲነሣሣ ምናሴ ካደረጋቸው ነገሮች ሁሉ የተነሣ፣ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ከነደደው ከአስፈሪው ቍጣው ገና አልበረደም ነበር።
“ይህ ሁሉ የደረሰብን በክፉ ሥራችንና በብዙ በደላችን ምክንያት ነው፤ አምላካችን ሆይ፤ አንተ ግን እንደ በደላችን ብዛት አልቀጣኸንም፤ ይልቁንም ቅሬታን ተውህልን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤ ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።
ወደዚያም ገብተው ወረሷት፤ ነገር ግን አልታዘዙህም፤ ሕግህንም አልጠበቁም፤ እንዲያደርጉት ያዘዝሃቸውን ከቶ አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ሁሉ ጥፋት በላያቸው አመጣህ።
ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ ፈሰሰ፤ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ነደደ፤ ዛሬ እንደሚታዩትም ማንም የማይኖርባቸው ፍርስራሾች አደረጋቸው።
አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው ዐለፉ፤ እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።
ስለዚህ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ በጽኑ ቍጣዬም አነድዳቸዋለሁ፤ ያደረጉትንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
ስለዚህ በቍጣ እመጣባቸዋለሁ፤ በርኅራኄ ዐይን አላያቸውም፤ ከሚመጣባቸው ነገር አላድናቸውም፤ ወደ ጆሮዬም ቢጮኹ አልሰማቸውም።”
ሰላም አለ በሚሉ አሕዛብ ላይ ግን በጣም ተቈጥቻለሁ፤ በመጠኑ ተቈጥቼ ሳለሁ፣ እነርሱ ግን ጥፋቱ እንዲብስ አደረጉ።’
ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት በኩል በመንፈሱ የላከውን ቃል ወይም ሕግ አልሰሙም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እጅግ ተቈጣ።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ያለ አንዳች ሐዘኔታ ጥፋት ላመጣባችሁ እንደ ወሰንሁ፣” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤
ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን እንኳ ገድለዋል፤ እናንተም አሁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም፤