Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘካርያስ 1:14

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፤ “ይህን ቃል ተናገር፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ ጽዮንና ስለ ኢየሩሳሌም እጅግ ቀንቻለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቅሬታ የሆኑት ከኢየሩሳሌም፣ የተረፉትም ከጽዮን ተራራ ይመጣሉና፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።

ሕዝቅያስም፣ “ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድን ነው?” ብሎ ነበር።

አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ ይላል አምላካችሁ።

ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።

ድምፅም፣ “ጩኽ” አለኝ፤ እኔም፣ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።

እግዚአብሔር እንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤ እንደ ተዋጊ በቅናት ይነሣል፤ የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤ ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል።

ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤ የድነትን ቍር በራሱ ላይ ደፋ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤ መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ።

ከተቀደሰው፣ ከተከበረውና ከፍ ካለው ዙፋንህ፣ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ኀይልህና ቅናትህ የት አለ? ገርነትህና ርኅራኄህ ከእኛ ርቀዋል።

ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሚቃጠል ቅናቴ በቀሩት ሕዝቦች ሁሉና በኤዶም ሁሉ ላይ ተናግሬአለሁ፤ ከልብ በመነጨ ደስታና በንቀት ተሞልተው የግጦሽ መሬቴን ይዘው ይበዘብዙት ዘንድ የራሳቸው ርስት አድርገውታልና።’

“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ስቦይ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።

እነሆ፤ እግዚአብሔር ስለ ምድሩ ይቀናል፤ ስለ ሕዝቡም ይራራል።

እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር የሚበቀል፣ በመዓትም የተሞላ ነው። እግዚአብሔር ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቍጣውን ያመጣል።

እግዚአብሔርም ከእኔ ጋራ ይነጋገር ለነበረው መልአክ ደስ በሚያሠኝና በሚያጽናና ቃል መለሰለት።

“ቀጥለህም እንዲህ እያልህ ስበክ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከተሞቼ እንደ ገና ብልጽግና ይትረፈረፍባቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ገና ጽዮንን ያጽናናል፤ ኢየሩሳሌምንም ይመርጣል።’ ”

እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁ። ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክም፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አሳይሃለሁ” አለኝ።

ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ አንድ ሰው ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አነቃኝ፤




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች