ከእኔ ጋራ ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ከእምነት የተነሣ ለሚወድዱን ሰላምታ አቅርቡልን። ጸጋ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።
ወንድሞቻችሁን ብቻ እጅ የምትነሡ ከሆነ ከሌሎች በምን ትሻላላችሁ? አሕዛብስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?
እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከእኔ ጋራ ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።
በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑ፣ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና፤ የሚጠቅመውስ በፍቅር የሚገለጽ እምነት ብቻ ነው።
ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።
በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለጢሞቴዎስ፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት፣ ሰላምም ይሁን።
የዚህ ትእዛዝ ዐላማ ግን ከንጹሕ ልብ፣ ከበጎ ኅሊና እንዲሁም ከእውነተኛ እምነት የሚገኝ ፍቅር ነው።
ጌታ ከመንፈስህ ጋራ ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።
ምክንያቱም በጌታ በኢየሱስ ያለህን እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ያለህን ፍቅር ሰምቻለሁ።
ጸጋ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።
ሽማግሌው፤ በእውነት ለምወድደው ለውድ ወዳጄ ለጋይዮስ፤