ውዴ ሆይ፤ አንቺ እንደ ቴርሳ የተዋብሽ፣ እንደ ኢየሩሳሌም ያማርሽ፣ ዐርማቸውን እንደ ያዙ ወታደሮችም ግርማን የተጐናጸፍሽ ነሽ።
የኢዮርብዓም ሚስትም ተነሥታ ወደ ቴርሳ ሄደች፤ የቤቱን መድረክ ወዲያው እንደ ተራመደች ልጁ ሞተ፤
ባኦስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ራማን መገንባቱን አቁሞ ወደ ቴርሳ ተመለሰ።
የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በቴርሳ ከተማ፣ በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ሃያ አራት ዓመትም ገዛ።
የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣ በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣ በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው።
እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፣ ብርቱ ምሽግ እንደ ሆናት አስመስክሯል።
ፍጹም ውብ ከሆነችው ከጽዮን፣ እግዚአብሔር አበራ።
ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ! ዐይኖችሽም እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እኔ ጥቍር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ ጥቍረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣ እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው።
አንቺ በገደል ዐለት ንቃቃት፣ በተራሮችም ባሉ መደበቂያ ስፍራዎች ውስጥ ያለሽ ርግቤ ሆይ! ፊትሽን አሳዪኝ፤ ድምፅሽንም አሰሚኝ፤ ድምፅሽ ጣፋጭ፣ መልክሽም ውብ ነውና።
ውዴ ሆይ፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ እንከንም አይወጣልሽም።
እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።”
እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣ እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?
በአጠገብሽ የሚያልፉ ሁሉ፣ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፤ “የውበት መደምደሚያ፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣ የተባለች ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ ራሳቸውን በመነቅነቅ፣ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያሾፋሉ።
የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሷ ላይ በሚሰበሰቡበት በዚያ ቀን፣ ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ የማይነቃነቅ ዐለት አደርጋታለሁ፤ ለማነቃነቅ የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን ይጐዳሉ።
ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሣሪያ የዚህ ዓለም መሣሪያ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኀይል ያለው ነው።
እንዲሁም ጕድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና እንከን አልባ የሆነች ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።
ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባሏ እንደ ተዋበች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።