አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?
የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤ ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው።
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤ ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ
አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣ የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም፣ በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።
አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ወዴት ሄደ? ዐብረንሽም እንድንፈልገው፣ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?
በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤ የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እንድንወድደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም።
ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም ከተማዋ በመላ፣ “ይህ ማነው?” በማለት ታወከች።
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።