ቅድሚያ ያለው ቅርብ የሥጋ ዘመድም ቦዔዝን፣ “እንግዲህ አንተው ራስህ ግዛው” ብሎ ጫማውን አወለቀ።
የወንድሙም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፣ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና “የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል” ትበል።
በጥንት ዘመን በእስራኤል የመቤዠትም ሆነ ንብረት የማስተላለፍ ጕዳይ የሚጸናው አንዱ ወገን ጫማውን አውልቆ ለሌላው ወገን ሲሰጠው ነው፤ በእስራኤል ዘንድ መሸጥም ሆነ መግዛት ሕጋዊነት የሚኖረው በዚህ ሁኔታ ነበር።
ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የአሊሜሌክን፣ የኬሌዎንንና የመሐሎንን ንብረት በሙሉ ከኑኃሚን ላይ ለመግዛቴ፣ በዛሬው ዕለት እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤