እኩለ ሌሊት ላይ ሰውየውን አንዳች ነገር አስደነገጠው፤ ገልበጥ ሲልም አንዲት ሴት እግርጌው ተኝታ አገኘ።
ቦዔዝ በልቶ ጠጥቶ ከጨረሰና ደስም ከተሠኘ በኋላ፣ ራቅ ካለው የእህል ክምር አጠገብ ለመተኛት ሄደ። ሩት በቀስታ ከአጠገቡ ደረሰች፤ እግሩንም ገልጣ ተኛች።
እርሱም፣ “አንቺ ማነሽ?” ሲል ጠየቀ። እርሷም፣ “እኔ አገልጋይህ ሩት ነኝ፤ መቤዠት የሚገባህ ቅርብ የሥጋ ዘመድ አንተ ነህና ልብስህን ጣል አድርግብኝ” አለችው።