ቀጥላም፣ “ ‘ወደ ዐማትሽ ባዶ እጅሽን አትመለሺ’ በማለት ይህን ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰጠኝ” አለቻት።
ሩት ወደ ዐማቷ እንደ ተመለሰች፣ ኑኃሚን፣ “ልጄ ሆይ፤ የሄድሽበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” ብላ ጠየቀቻት። ሩትም ቦዔዝ ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት፤
ኑኃሚንም፣ “ልጄ ሆይ፤ የሚሆነውን ነገር እስክታውቂ ድረስ ታገሺ፤ ጕዳዩ ዛሬውኑ እልባት ካላገኘ ሰውየው አያርፍም” አለቻት።