ኑኃሚንም ምራቷን ሩትን፣ “የእኔ ልጅ፤ እንዲህ ካልሽማ ከሴት ሠራተኞቹ ጋራ ዐብሮ መሄድ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው አዝመራ ብትሄጂ ጕዳት ሊያገኝሽ ይችላልና” አለቻት።
የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።
አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣ የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም፣ በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
ጴጥሮስ በግቢው ውስጥ በታችኛው በኩል ሳለ፣ ከሊቀ ካህናቱ የቤት ሠራተኞች አንዲቱ መጣች፤
ከዚያም ሞዓባዊቷ ሩት፣ “ደግሞም፣ ‘እህሌን ሁሉ ዐጭደው እስኪጨርሱ ድረስ ከሠራተኞቼ አትለዪ!’ ብሎኛል” አለቻት።
ስለዚህ የገብሱና የስንዴው አዝመራ ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ፣ ሩት የቦዔዝን ሴቶች ሠራተኞች ተጠግታ ቃረመች፤ ከዐማቷም ጋራ ኖረች።