በመልካም መስተንግዶው እኔና በዚህ የምትገኘዋ መላዋ ቤተ ክርስቲያን ደስ የምንሰኝበት ጋይዮስ፣ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የከተማዪቱ ግምጃ ቤት ሹም የሆነው ኤርስጦስ፣ ወንድማችንም ቍአስጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። [
ከረዳቶቹም ሁለቱን፣ ጢሞቴዎስንና ኤርስጦንን፣ ወደ መቄዶንያ ልኮ እርሱ ራሱ ግን በእስያ አውራጃ ጥቂት ቀን ተቀመጠ።
ወዲያውም በከተማው ሁሉ ሁከት ተነሣ፤ ሕዝቡም አንድ ላይ በማበር የመቄዶንያ ተወላጅ የሆኑትንና ከጳውሎስ ጋራ ይጓዙ የነበሩትን ጓደኞቹን፣ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ይዘው ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ እየሮጡ ገቡ።
የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሱሲጴጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ እንዲሁም ጢሞቴዎስ ዐብረውት ሄዱ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን። አሜን።]
ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ከእናንተ ማንንም ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀርቷል፤ ጥሮፊሞስም ስለ ታመመ በሚሊጢን ትቼዋለሁ።