የፈረሶቹ ኀይል በአፋቸውና በጅራታቸው ላይ ነበር፤ ጅራታቸውም እባብ ይመስል ነበር፤ ራስ ስላላቸው ጕዳት የሚያደርሱት በርሱ ነበር።
ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣ ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።
ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም።
እንደ ጊንጥም ያለ፣ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ ደግሞም ሰዎችን ዐምስት ወር የሚያሠቃዩበት ኀይል በጅራታቸው ላይ ነበር።
ከአፋቸው በወጡት፣ በሦስቱ መቅሠፍቶች፣ ማለት በእሳቱ፣ በጢሱና በዲኑ አንድ ሦስተኛው የሰው ዘር ተገደለ።
በእነዚህ መቅሠፍቶች ሳይገደሉ የቀሩት ሰዎች አሁንም ከእጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትን እንዲሁም ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከዕንጨት የተሠሩትን ጣዖቶች ማምለክ አልተዉም፤