የበለስ ዛፍ በብርቱ ነፋስ ስትወዛወዝ ያልበሰለው ፍሬ ከርሷ እንደሚረግፍ፣ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ።
ፍሬው በጮርቃነት እንደ ተለቀመበት የወይን ተክል፣ አበባውም እንደ ረገፈበት የወይራ ዛፍ ይሆናል።
የሰማይ ከዋክብትና ሰራዊታቸው፣ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።
ምድሪቱ አለቀሰች፤ መነመነች፤ ሊባኖስ ዐፈረች፤ ጠወለገች፤ ሳሮን እንደ ዓረባ ምድረ በዳ ሆነች፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።
የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤ የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣ ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣ ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።
ለዳዊት ቤት፣ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፣ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።
አንተን በማጠፋ ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ፤ ፀሓይን በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።
እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ ‘ዛፉን ቍረጡ፤ ቅርንጫፎቹን ጨፍጭፉ፤ ቅጠሎቹን አራግፉ፤ ፍሬውንም በትኑ፤ ከሥሩ ያሉት እንስሳት፣ በቅርንጫፎቹም ላይ ያሉት ወፎች ይሽሹ።
ወደ ሰማይ ሰራዊት እስኪደርስ ድረስ አደገ፤ ከከዋክብት ሰራዊትም የተወሰኑትን ወደ ምድር ጣለ፤ ረጋገጣቸውም።
ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማ፤ ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።
ምሽጎችሽ ሁሉ ሊበሉ እንደ ደረሱ የበኵራት በለስ ፍሬ ናቸው፤ በሚወዛወዙበት ጊዜ፣ ፍሬዎቹ በበላተኛው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።
“ወዲያውኑ ከእነዚያ ከመከራው ቀናት በኋላ፣ “ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፤ ጨረቃ ብርሃኗን ትከለክላለች፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናጋሉ።’
ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናወጣሉ።’
“በፀሓይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክት ይሆናል፤ ከባሕሩና ከሞገድ ድምፅ የተነሣ፣ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ይጨነቃሉ፤ ይታወካሉም።
ዐምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀውንም ኮከብ አየሁ፤ ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።