የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ፣ ሁለተኛው በሬ ይመስሉ ነበር፤ ሦስተኛው የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው ደግሞ የሚበርር ንስር ይመስል ነበር።
አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?
ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣ የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
አገር ስታምፅ፣ ገዦቿ ይበዛሉ፤ አስተዋይና ዐዋቂ ሰው ግን ሥርዐትን ያሰፍናል።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።
ፊታቸውም እንዲህ ነበር፤ አራቱም እያንዳንዳቸው የሰው ፊት ነበራቸው፤ በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፣ በግራ በኩልም የበሬ ፊት ነበራቸው፤ እያንዳንዳቸውም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።
በአራቱ ጐኖቻቸው ባሉት ክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ ነበራቸው። አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው፤
እያንዳንዱም ኪሩብ አራት አራት ፊት ነበሩት፤ ይኸውም አንደኛው ፊት የኪሩብ፣ ሁለተኛው የሰው ፊት፣ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፣ አራተኛውም የንስር ፊት ነበር።
እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊት፣ አራት አራት ክንፍ፣ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰውን እጅ የሚመስል ነበራቸው።
“የመጀመሪያው፣ አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ተመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግሩ እንዲቆም ከምድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ የሰውም ልብ ተሰጠው።
እንደ ንስር መጥቀህ ወደ ላይ ብትወጣ፣ ጐጆህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤ ያደነውን እስኪያነክት፣ የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣ እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።”
እንደ አንበሳ አድፍጠዋል፤ እንደ እንስቲቱም አንበሳ አድብተዋል፤ ሊቀሰቅሳቸውስ የሚችል ማን ነው? “የሚባርኩህ ቡሩክ፣ የሚረግሙህም ርጉም ይሁኑ።”
ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ፤ በአስተሳሰባችሁ ግን ጕልማሶች ሁኑ።
እግዚአብሔር እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋውን የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፣ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤
ደግሞም በዙፋኑ ፊት እንደ መስተዋት የጠራ የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑ መካከል፣ በዙሪያውም ከፊትና ከኋላ በዐይን የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።
በጉ ሁለተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር፣ “ና!” ሲል ሰማሁ።
በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር፣ “ና!” ሲል ሰማሁ። እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ ጥቍር ፈረስ ቆሞ አየሁ፤ ተቀምጦበት የነበረውም በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር።
በጉ አራተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ አራተኛው ሕያው ፍጡር፣ “ና!” ሲል ሰማሁ።