ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤ በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤
ዳዊትም በዜማ መሣሪያ፣ ማለትም በመሰንቆ፣ በበገናና በጸናጽል እየታጀቡ የደስታ ዜማዎችን የሚያዜሙ መዘምራንን ከወንድሞቻቸው መካከል እንዲሾሙ ለሌዋውያኑ መሪዎች ነገራቸው።
በዚህ ሁኔታ መላው የእስራኤል ሕዝብ በሆታ ቀንደ መለከትና እንቢልታ እየነፉ፣ ጸናጽል እየጸነጸሉ፣ መሰንቆና በገና እየደረደሩ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አመጡ።
ንጉሥ ሕዝቅያስም በዳዊት፣ በንጉሡ ባለራእይ በጋድና በነቢዩ በናታን በተሰጠው መመሪያ መሠረት ሌዋውያኑን ጸናጽል፣ በገናና መሰንቆ አስይዞ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መደባቸው፤ ይህም በነቢያት አማካይነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትእዛዝ ነበር።
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።
አምላኬ ሆይ፤ ስለ ታማኝነትህ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፤ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።
እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣ በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ ተድላና ደስታ፣ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በርሷ ይገኛሉ።
መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችም በበጉ ፊት በግንባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም የቅዱሳን ጸሎት የሆኑትን በገናና ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር።