ለኀጢአተኞች ጕድጓድ እስኪማስላቸው ድረስ፣ እርሱን ከመከራ ታሳርፈዋለህ።
እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊፈርድ ይችላል? ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል? እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤
የአጭበርባሪዎች ክፋት በከበበኝ ጊዜ፣ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
አሕዛብ በቈፈሩት ጕድጓድ ገቡ፤ እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።
የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን? እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤ ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣ በፊትህ ቆሜ፣ ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ።
ሊይዙኝ ጕድጓድ ስለ ቈፈሩ፣ ለእግሮቼም በስውር ወጥመድ ስለ ዘረጉ፣ በድንገት ወራሪ ስታመጣባቸው፣ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።
እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
ስለዚህ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ገና ቀርቶለታል፤
ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።
አሕዛብ ተቈጥተው ነበር፤ የአንተም ቍጣ መጣች፤ በሙታን ላይ የምትፈርድበት፣ ለባሮችህ ለነቢያት፣ ለቅዱሳንና ስምህን ለሚፈሩት፣ ለታናናሾችና ለታላላቆች ዋጋቸውን የምትሰጥበት፣ ምድርንም ያጠፏትን የምታጠፋበት ዘመን መጣ።”
ከዚያም፣ “ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ ሆነው የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ። መንፈስም፣ “አዎ፣ ሥራቸው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ያርፋሉ” ይላል።