በአጠገብህ ሺሕ፣ በቀኝህም ዐሥር ሺሕ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፉ፤ ሰዎችና እንስሳት በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች ከምድር ላይ ጠፉ፤ ኖኅና ከርሱ ጋራ በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ።
ስለዚህ የምትታመኑት ሁሉ፣ በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣ እርሱ አጠገብ አይደርስም።
እታደግሃለሁ፤ በእኔ ታምነሃልና በሕይወት ታመልጣለህ እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ”
“አሁንም እነሆ፤ ልክ እግዚአብሔር እንዳለው ይህን ለሙሴ ከተናገረበት ጊዜ አንሥቶ እስራኤል በምድረ በዳ ሲንከራተት እኔን አርባ ዐምስት ዓመት በሕይወት ጠብቆ አኑሮኛል፤ ይኸው ዛሬ ሰማንያ ዐምስት ዓመት ሆነኝ።