እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ለአገልጋዮችህም ራራላቸው።
ለእነርሱም ሲል ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፤ እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቍጣው ተመለሰ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፣ ለአገልጋዮቹም ይራራላቸዋል።
በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤ በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል?
አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?
የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤ ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤ ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤
ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣ ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል ናት።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን? ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው?
ግብጻውያን፣ ‘በተራሮቹ ላይ ሊገድላቸው፣ ከገጸ ምድርም ሊያጠፋቸው ስለ ፈለገ ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከክፉ ቍጣህ ተመለስ፤ ታገሥ፤ በሕዝብህም ላይ ጥፋት አታምጣ።
ከዚያም እግዚአብሔር ታገሠ፤ በሕዝቡም ላይ አመጣባቸዋለሁ ያለውን ጥፋት አላመጣባቸውም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን? ስለ ባሮችህ ስትል፣ ስለ ርስትህ ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።
ከነቀልኋቸው በኋላ ግን መልሼ እምራቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውንም ወደ ገዛ አገራቸውና ወደ ገዛ ርስታቸው መልሼ አመጣቸዋለሁ።
“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ስቦይ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።
እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ። እግዚአብሔርም “ይህ አይፈጸምም” አለ።
እግዚአብሔር ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ ጌታ እግዚአብሔር፣ “ይህም ደግሞ አይፈጸምም” አለ።
እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቍጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በምሕረት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ በዚያም ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ባረፉ ጊዜም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በብዙ ሺሕ ወደሚቈጠሩት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር።
ኀይላቸው መድከሙን፣ ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል።